top of page



መሸፈኛ 2
“… በውስጥም በውጭም በቅጥራን ለቅልቃት” ዘፍ. 6፡14 ሀብታሙ አብርደው በጡረ ይህ በመጻሕፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኝና ብዙ ሰዎች ልብ ሳይሉት የሚያልፉት ምስጢር ነው። በዘፍጥረት መጽሐፍ እግዚአብሔር ኖኅን መርከቧን እንዲሰራ ሲያዘው፣ በውስጥም በውጭም በቅጥራን እንዲለቀልቃት ነግሮት ነበር። ቅጥራን ወፍራም ፈሳሽ የማሸጊያ ቁስ ሆኖ ውኃው ወደ መርርከቢቱ ውስጥ ሰርጎ እንዳይገባ የሚከላከል ነው። በመርከቢቱ ውስጥ ያሉት ሁሉ ከመጥፋት የዳኑት መርከቢቷ ውሃ የማታስገባ ሆና በመሠራቷ ጭምር ነበር ይህም በውስጥም በውጭም ከተለቀለቀችው ቅጥራን የተነሳ ነው። ከዚያም ከበርካታ ዓመታት በኋላ በዘጸአት መጽሐፍ ሕፃኑ ሙሴ በአባይ ወንዝ ላይ በትንሿ ቅርጫት ውስጥ በተቀመጠ ጊዜ፣ እናቱ ውኃው ወደ ቅርጫቱ ሰርጎ እንዳይገባ እና ህጻኑን እንዳይገድለው ቅርጫቷን በቅጥራን


መሸፈኛ
ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 3 ብዙውን ጊዜ የሰው ልጅ ነገሮች ሁሉ የተበላሹበት ምዕራፍ ተደርጎ ይወሰዳል። ሆኖም ኝ በዚያ ውድቀትና ሀፍረት ውስጥ አስቀድሞ የተገለጠው የምስራች (የወንጌል) ብርሃን ምሥጢር ይገኛል። አዳምና ሔዋን ኃጢአት በሠሩ ጊዜ መጀመሪያ የተሰማቸው ስሜት ሀፍረት ነበር። ያደረጉትም ነገር የወደቀውን የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ምላሽ ነበር፤ ተሸሸጉ። የበለስ ቅጠሎችን ሰፉ። በራሳቸው ጥረት ሃፍረታቸውን ለመሸፈን ሞከሩ። ገና የእግዚአብሔርን ድምጽ እንኳን ከመስማታቸው በፊት፣ የሰው ልጅ ራሱን ከሃፍረቱ ለመሸፈን ጥረት መጀመሩን እንመለከታለን። ቀጥሎ የሆነው ነገር ግን እጅግ አስገራሚ ነው። እግዚአብሔር የእነርሱን የበለስ ቅጠል አልተቀበለም። መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር፦ “እግዚአብሔር አምላክ ለአዳምና ለሚስቱ የቁርበትን ልብስ አደረገላቸው፤ አለበሳቸውም”


በክርስቶስ ፍቅር የታነጸ ጋብቻ፡
"ሚስቶች ሆይ፥ ለጌታ እንደምትገዙ ለባሎቻችሁ ተገዙ" ኤፌሶን 5፡22 ቅዱስ ጳውሎስ በኤፌሶን 5፡22 ላይ "ሚስቶች ሆይ፥ ለጌታ እንደምትገዙ ለባሎቻችሁ ተገዙ" ሲል የጻፈው ቃል፣ በዘመናችን ብዙ ጊዜ በተሳሳተ መንገድ ሲተረጎም ይስተዋላል። ነገር ግን በካቶሊክ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ መሰረት፣ ይህ ቃል የጭቆና ሳይሆን የቅዱስ ቁርባን ፍቅር መግለጫ ነው። ይህንን ጥቅስ ለመረዳት ከላይ ያለውን ቁጥር 21 ቀድሞ ማንበብ ያስፈልጋል፡ "ክርስቶስ ን በመፍራት እርስ በርሳችሁ ተገዙ።" የክርስቲያን ጋብቻ መሰረቱ ባልና ሚስት ለክርስቶስ ያላቸው ፍቅር ነው። ሚስት ለባሏ የምታሳየው መገዛት፣ ባል ሚስቱን እንደ ገዛ አካሉ አድርጎ እስከ መስዋዕትነት ድረስ ከመውደዱ (ቁጥር 25) ተነጥሎ አይታይም። ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጋብቻን "ታላቅ ምስጢር" (Sac


"ከእሳቱ የተለየ ፍም አይሞቅም"
ሀብታሙ አብርደው በጡረ ከጥቂት ሳምንታት በፊት “ሰዎች ለምን ከቤተክርስቲያን ይርቃሉ?” የሚል ጥያቄ በገጼ ላይ አጋርቼ ነበር። ሰሞኑን አንድ ሰው ወደ እኔ ቀረብ ብሎ እንዲህ አለኝ፦ "ያጋራኸውን ጽሁፍ አይቼዋለሁ። እኔ እኮ አሁንም እግዚአብሔርን እወደዋለሁ፤ የራቅኩት ከቤተክርስቲያን እንጂ ከእግዚአብሔር አይደለም።" አለኝ። ምክንያት ያለውንም ይዘረዝርልኝ ጀመር። በቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ ሰዎች የሚያደርጉትን ነገር እርሱ ወደቢተክርስቲያን እንዳይመጣ እንዳደረገውም አስረዳኝ። እኔም ሌላ ጥያቄ አቀረብኩለት፦ "ለመሆኑ አንተ ፍጹም ነህን?" እርሱም "በየሰንበቱ እና በዓላቱ ወደ ቤተክርስቲያን ባልሄድም፣ ከሚያዘወትሩት ግን ሳልሻል አልቀርም" ሲል መለሰልኝ። ቤተክርስቲያን የተሰራችው ለፍጹማን አይደለም። ቢሆን ኖሮ ማንም የመግባት ብቃት ባልነበረው ነበር


“ኤል ሮኢ” የሚያየን አምላክ
ሀብታሙ አብርደው በጡረ ሰዎች በሚገፉባቸው እና ረዳት የለሽ የሆኑ በሚመስላቸው ሥፍራዎች ሁሉ የአጋር ታሪክ ይገለጣል። አጋር በአብርሃም ቤት ውስጥ የምትኖር ግብፃዊት አገልጋይ ነበረች፤ ከቤተዘመዶቿ እማ ከቀየዋ ርቃ፣ ተገልላና ምርጫ አጥታ የኖረች ናት። ምንም ነገር በእርሷ ፈቃድ አይደረግላትም አይደረግባትም። ውሳኔዎች ያለ እሷ ስምምነት ከበላዩዋና በዙሪያዋ በሚኖሩ ሰዎች ነበር የሚወሰኑት። ለራሷ ባልሆነ ዓላማ ጥቅም ላይ ውላ፣ በማትፈለግበት ጊዜ ደግሞ የተገፋች ነበረች፣ አጋር ብዙ የተገፉ ነፍሳት እንደሚያደርጉት ከሥቃይ፣ ከፍርሃትና መልስ ከሌላቸው ጥያቄዎች በቀር ምንም ሳትይዝ ራሷን በስደት ጎዳና ላይ አገኘችው። በስደት ወደ በረሃ ስትገባ የተሸከመችው ረሃብንና ድካምን ብቻ አልነበረም፤ መገፋትንና ያለመታየት ሕመምን ጭምር ነበር። ይሁን እንጂ፣ በዚያው


ጋብቻ የማይፈርስ ቃልኪዳን
ይህ ጽሑፍ በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ (Catechism of the Catholic Church - CCC 1601-1666) ላይ በመመስረት ስለ ምስጢረ ተክሊል የተዘጋጀ አጭር ማብራሪያ ነው። ጋብቻ (ምሥጢረ ተክሊል) በፈጣሪ ፈቃድ የተመሰረተ፣ በወንድና በሴት መካከል የሚደረግ የህይወትና የፍቅር አንድነት ነው። እግዚአብሔር ሰውን የፈጠረው በፍቅር ስለሆነ፣ ለፍቅርም ጠርቶታል። ጋብቻ በሰው ልጅ ተፈጥሮ ውስጥ የታተመ የፍቅር ጥሪ ነው። ካቴኪዝም እንደሚያስተምረው ጋብቻ ውል ሳይሆን ቅዱስ "ምስጢር" (Sacrament) ነው። ይህም ማለት ባልና ሚስት በጋብቻቸው ውስጥ የእግዚአብሔርን ጸጋ ይቀበላሉ ማለት ነው። ጋብቻ የሁለት ሰዎች ስምምነት ብቻ ሳይሆን፣ እግዚአብሔር የሚገኝበት ቅዱስ ጥምረት ነው። ባልና ሚስት እርስ በእርሳቸው እንዲቀደሱና ዓለምን


የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ለምሥጢረ ተክሊልና ለቤተሰብ
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ መገለጥ (ልደት) ለሰው ልጅ ድኅነት የተከናወነ ታላቅ ምሥጢር ብቻ ሳይሆን፣ ለክርስቲያናዊ ጋብቻና ለቤተሰብ ሕይወት መሠረትና ነው። በካቶሊክ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት፣ ልደት የቤተሰብን ክብር ከፍ ያደረገበትና የምሥጢረ ተክሊልን ትርጉም ያደሰበት ክስተት ነው። 1. ቤተሰብን "አነስተኛ ቤተክርስቲያን" (Domestic Church) እግዚአብሔር ወልድ ወደዚህ ዓለም ሲመጣ በቤተሰብ ውስጥ መወለድን መረጠ። ቅዱስ ዮሴፍና ቅድስት ድንግል ማርያም ሕፃኑን ኢየሱስን ተንከባክበው ባሳደጉበት በናዝሬቱ ቅዱስ ቤተሰብ አማካኝነት፣ እያንዳንዱ ክርስቲያን ቤተሰብ እግዚአብሔር የሚኖርበት "አነስተኛ ቤተክርስቲያን" የመሆን ጸጋን አግኝቷል። "የናዝሬቱ ቅዱስ ቤተሰብ ለእያንዳንዱ ክርስቲያን ቤተሰብ ፍጹም አምሳያና መመሪያ ነው።" (C


ጾም ምንድ ነው?
የነፍስ እና የሥጋ ኅብር የሆነው ሰው ስብዕናው አምስት ማንነቶችን ያዘለ ነው። ሰው የአካላዊ፣ ስሜታዊ፣ ሥነልቦናዊ፣ መንፈሳዊ እና ማህበራዊ ማንነቶች ጥምር ነው፡፡ ኣካላዊ ማንነታችን ውበት እና ገጽታችን ላይ እንድናተኩር የሚፈልገው ማንነታችን ነው፡ ስሜታዊ ማንታችን ደግሞ ደስታ፣ ፈንጠዚያ እና መዝናናትን ማዘውተር ትፈልጋለች። ስነልቦችን የሚያውቀውና የሚማረው ማንነታችን ሲሆን ባወቀ እና በተማረ ቁጥር ደግሞ ለዝና እና ለክብር ይሸነፋል፡ ማሕበራዊ ማንነታችን ደግሞ ከምንኖርበት አካባቢ ጋር የተቆራኘ፣ ከቤተሰብ፣ ከዘመድ ወዳጅ፣ ከባልንጀራ እና ባጠቃላይ ከሰው፣ ከእንስሳ እና ከአካባያችን ጋር ያለንን ግንኙነት የምታካትት ናት። መንፈሳዊ ማንነታችን ግን ዘወትር እግዚአብሔርን የምትፈልግ ናት፡፡ እነዚህን የማንነታችንን ንዑሳን ክፍሎች ከተመለከትን ጾም ምን


ከእናንተ እያንዳንዱ የሌላውን ሸክም ይሸከም
በሀብታሙ አብርደው በጡረ የ2007 ዓ.ም. የቅዱስ ገብርኤል ኖቬናን በማስመልከት የተዘጋጀ ታሕሣሥ 9 ቀን 2007 ዓ.ም. “ከእናንተ እያንዳዱ የሌላውን ሸክም ይሸከም፡፡ እንዲሁም የኢየሱስን ሕግ ትፈጽማላችሁ፡፡” (ገላ. 6፡2) ቅዱስ ጳውሎስ ለገላትያ ሰዎች የጻፈላቸው ይህ መልዕክት ሁለት ዋና ዋና ክፍሎች አሉት፡፡ እነሱም “የሌላውን ሸክም መሸከም” እና “የኢየሱስን ሕግ መፈጸም” ናቸው፡፡ ሸክም ምንድን ነው? ሰዎች ስንባል በዚህ ዓለም በምንኖርበት ጊዜ ሁሉ ሁለት ዓይነት ሸክሞች አሉብን፡፡ አንደኛው ማንም ሊያግዘን የማይችልና እራሳችን ብቻ የምንወጣው ነው፡፡ ለምሳሌ ታታሪ ሠራተኛ መሆን፣ ታማኝ ባል ወይም ሚስት መሆን፣ መልካም ወላጅ መሆን እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ ሌላው ደግሞ ሌሎች ሊያግዙን እኛም ሌሎችን ልናግዛቸው የምንችላቸው ነው፡፡ ለ


የእግዚአብሔር ጸጋ
ለቅዱስ አንጦንዮስ ዓመታዊ ክብረ በዓል ነጋዲያን የቀረበ ሰኔ 3 ቀን 2007 ዓ.ም. ልደታ ማርያም (ካቴድራል) አዲስ አበባ ከፍጥረት አንሥቶ የነበረውን የሰው ልጅ ታሪክ ስንመረምር አዳምና ሔዋን በመጀመሪያ እግዚአብሔር በሚመላለስበት በዚያ በእግዚአብሔር ጸጋ ሙላት ይኖሩ ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ፍርሃት፣ ጭንቀት፣ ኀፍረት የሚባሉ ነገሮች አያውቋቸውም ነበር፡፡ ኋላ ላይ ሰው በወደቀ ጊዜ የእግዚአብሔር ጸጋ ከላያቸው ላይ ተገፈፈ፡፡ መፍራት፣ መሸሽ፣ መደበቅ ሀብታቸው ሆነ፡፡ አዳምም ትላንት “ከሥጋዬ የተገኘች ሥጋ ከአጥንቴ የተገኘች አጥንት” ብሎ በደስታ ባዜመላት በሔዋን ፊት ዕርቃኑን ሊቆም አልተቻለውም፡፡ ኀፍረቱን ይሸፍንበት ዘንድ ቅጠል ሽምጠጣ ገባ፡፡ ሔዋንም እንዲሁ፡፡ እግዚአብሔር ግን የሰው ልጅን ይወደው ነበርና ከበግ ለምድ ልብስን ሰፍቶ አለበ


አለመግባባታችንንም ቢሆን ለትዳራችን እድገት ማዋል እንችላለን
ባልና ሚስት በመካከላቸው አለመግባባት ሳይከሰት ሊኖሩ አይችሉም፡፡ በኑሯቸው ውስጥ በተለያዩ ምክንያቶች መጋጨት እና መጣላት ያጋጥሟቸዋል፡፡ ነገር ግን አለመግባባት በሚከሰት ጊዜ ፍትሐዊ እና ለፍቅራችሁ ገንቢ በሆነ መልኩ መወጣት ይቻላል፡፡ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ጠቃሚ ሃሳቦች ብታነቧቸው ይጠቅሟችኋል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ አለመግባባቶች የሚካረሩት በአሸናፊነት ሥነልቦና የሚመሩ በመሆኑ ነው፡፡ የመነጋገራችሁ ዋና ዓላማ እርሷን ወደ አንተ ወይም አንተን ወደ እርሷ ሃሳብ ለመውሰድ የሚደረግ ትግል መሆን የለበትም፡፡ ይልቅስ ሁለታችሁንም ከዚህ በፊት ወደ አልነበራችሁበት አንድ አዲስ ምእራፍ የሚያሸጋግር እንጂ፡፡ በመሆኑም ሁለታችሁም በእኩል ደረጃ እየተደማመጣችሁ መነጋገር አለባችሁ እንጂ ውይይታችሁ በማእረግ ተዋረድ አካሄድ መሠረት መከናወን የለበትም፡፡ ይህም ማለት


የጋብቻ ቀለበታችንን በግራ እጃችን የምናደርገው ለምንድ ነው?
የጋብቻ ቀለበታችንን በግራ እጃችን የምናደርገው ለምንድ ነው? የቀለበት ጣታችንስ ለምን ተመረጠ? ዛሬ በጥቂት የዓለማችን ክፍል ካልሆነ በስተቀር የጋብቻ ቀለበት የሚደረገው በግራ እጅ የቀለበት ጣት ላይ ነው፡፡ በርካታ ሃይማኖታዊ ሥነሥርዓቶችም ይህንኑ ተግባራዊ እያደረጉ ቆይተዋል፡፡ ለመሆኑ ይህ የጋብቻ ቀለበትን በግራ እጅ የቀለበት ጣት ላይ የማጥለቅ ልማድ የተገኘው ከየት ነው? መሠረታዊ እምነቱስ ምንድን ነው? የጋብቻ ቃል ኪዳንን በማስመልከት በጣት ላይ ቀለበት ማድረግ የተጀመረው በጥንት ግብጻውያን ዘመን መሆኑን ታሪክ ይናገራል፡፡ ይኸውም ከክርስቶስ ልደት 3000 ዓመታት አስቀድሞ መሆኑ ነው፡፡ ጥንታውያን ግብጻውያን በአባይ ወንዝ ዳርቻዎች ላይ የበቀሉ ቄጤማዎችን በመጎንጎን በጣታቸው ላይ እንደ ቀለበት፣ በእጃቸውም ላይ እንደ አምባር በማሰር እና የጋ


ወደ ጋብቻ ለመግባት ስናስብ ከሁሉ አስቀድመን ቦታ ልንሰጠው የሚገባን ነገር ምንድን ነው?
ዛሬ እኛ ልንገባበት እና ቀሪ ዘመናችንን በቃል ኪዳን ልንመራበት የምንፈልገውን ጋብቻ የመሠረተው እና የቤተሰብ ሕይወት ደራሲ እግዚአብሄር ነው፡፡ ስለዚህ ያማክረን ዘንድ ወደ ጓደኛ፣ ዘመድ አዝማድ ወይም አማካሪ አና ባለሞያ ከመሄዳችን አስቀድመን በርከክ ነው ማለት ያለብን፡፡ ወደ አደግንባት፣ ምናልባትም ሕይወታችንን ሀ ብለን ወደጀመርንባት፣ ምናልባትም ደግሞ የመጀመሪያውን ምሥጢራት ወደተቀበልንባት ታቦት ሥር ድፍት ብለን የልባችንን ሀሳብ ከማንም በፊት ለእግዚአብሄር ማቅረብ ይገባናል፡፡ በጽሞና በፊቱ በቂ ጊዜ ማሳለፍ እጅግ ይጠቅመናል፡፡ የዛሬው ባለቤቴ በዛን ጊዜ አብሮኝ በአንድ ቁምስና በዝማሬ ያገለግል የነበረው የአገልግሎት የቅርብ ጓደኛዬ የፍቅር ግንኙነት እንድንጀምር ጥያቄ ያቀረበልኝ ዕለት መጀመሪያ ያደረግነው ነገር ቢኖር ምንም መልስ ሳንሰጣጥ


ሳላስበው ከፈጸምኩት ተግባር ብዙ የተማርኩበት አጋጣሚ
ጊዜው በአገራችን አቆጣጠር በ2003 ዓ.ም. ነው፡፡ ሥፍራው በስዊዘርላንድ ዙሪክ፡፡ አርብ ዕለት እንደወትሮዬ በማለዳ ተነሥቼ ወደ ሥራ ገባሁ፡፡ ከወትሮው የተለየ ነገር ይገጥመኛል የሚል ጥርጣሬውም አልነበረኝም፡፡ ረፋዱ ላይ ከምሠራበት ክፍል ሆኜ ቁልቁል በመስኮት ወደ ውጭ ስመለከት ሁለት በመሥሪያ ቤቱ ያልተለመዱ እንግዳ ሰዎችን ተመለከትኩ፡፡ ውስጤ የሆነ ነገር ሽብር ቢልብኝም ብዙም ቁም ነገር ሳልለው ወደ ሥራዬ ተመለስኩ፡፡ ሳይዘገይ በመስኮት የተመለከትኳቸው ሰዎች ከሌሎች ሰዎች ጋር ሆኜ ወደ ምሠራበት ክፍል ዘልቀው ስሜን ከነአባቴ ጠሩኝ፡፡ አቤት ብዬ ወደ እነርሱ ቀረብኩ፡፡ ፖሊስ መሆናቸውን ከነገሩኝ በኋላ መታወቂያዬን እንዳሳያቸው ጠየቁኝ፡፡ አሳየኋቸው፡፡ ካመሰገኑኝ በኋላ በደሞዝ ተቀጥሬ የመሥራት ፈቃድ ያለኝ እንደሆነ ጠየቁኝ፡፡ የለኝም በድብቅ


ውሃ ውይንስ የወይን ጠጅ?
አንድ ወዳጄ ነው፡፡ አንድ ቀን ወትሮ እንደምናደርገው በእርሱ መኪና የሆነ ሥራ ለማስፈጸም እየተጓዝን ሳለ በትዳሩ ውስጥ የገጠመውን ችግር አጫወተኝ፡፡ የውልሀ ሀብታሙ ሁለታችንም አግብተናል፡፡ ሁለታችንም ደግሞ ያገባነው ሴቶችን ነው፡፡ አንተ ደግሞ በትንሹ ለሰባት ዓመታት ያህል ትዳርን ከእኔ ቀድመህ ታውቀዋለህ፡፡ እስኪ ንገረኝ ትዳር ከመመሥረትህ በፊት የነበሩህ እነዛ ሞቃት የፍቅር ስሜቶች ይቀዘቅዛሉ እንዴ? ማለቴ ይጠፋሉ፣ ወይ ይቀየራሉ? አለኝ፡፡ ምንም እነኳን ሁለታችንም በተለያዩ ጊዜያት የየቤታችንን ችግሮች የምናወራ እና የመፍትሔ ሃሳብም በጋራ የምንፈልግ ቢሆንም የዛሬው ጥያቄው ግን አስደንግጦኛል፡፡ እናም “ምን አልከኝ?” አልኩት፡፡ በትዳሬ ላይ ያለኝ የፍቅር ስሜት ጭራሽ ቀዝቅዟል፡፡ አሁን ላይ ባለቤቴን ምንም አላፈቅራትም፡፡ ለስሜቷም ግድ የለኝም


“እግዚአብሔር አንድ ያደረገውን ማንም አይለየው”
ትዳር በካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ትዳር ራስን ለመተካትና አዲስ ሕይወትን ለመፍጠር ከእግዚአብሔር ጋር ትበብር የምናደርግበት በዚህች ዓለም የሚከናወን የወንድና የሴት የሠመረ የፍቅር ጥምረት ነው፡፡ አዲስ ሕይወትን የመፍጠር ሂደቱ ምሉዕ የሚሆነው ከእግዚአብሔር ጋር በሚደረግ ፍጹም ትብብር በመሆኑ መንፈሳዊ ባኅሪም አለው፡፡ ትዳር በወንድና በሴት መካከል እስከ ሞት ጸንቶ እነዲቆይ የሚመሠረት የፍቅር ግንኙነት ነው፡፡ ጥምረቱ የሚሰፋበት ሰበዝ ደግሞ እግዚአብሔር ነው፡፡ በትዳር ውስጥ የእግዚአብሔር ሚና ባለትዳሮቹን በማገናኘት ላይ ብቻ የተወሰነ አይደለም፡፡ ሁለቱን በፍቅር የሚያስተሳስር ማሰሪያ ሆኖ ለዘላለም አብሯቸው የሚኖር ነው፡፡ በእርሱ እነርሱ ይተሳሰራሉ፡፡ በዚህም ምክንያት በምድር የሚገኝ ማንኛውም ኃይል፣ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ እንደራ
bottom of page