top of page

እኛ ማን ነን?

የዚህ ድረገጽ ባለቤቶች ሀብታሙ አብርደው እና ወይንሸት ደምሴ ነን፡፡ ሁለታችንም ከጠንካራ ካቶሊካውያን ቤተሰቦች ተወልደን በካቶሊካዊት ሥርዓት ተጠምቀን ቅዱሳት ቁርባንን፣ ሜሮንን እና የተክሊልን ምሥጢራት በአዲስ አበባ ልደታ ማርያም ቁምስና ካቴድራል ተቀብለናል፡፡ በቁምስናችን በመዘምራንነት ለረጅም ጊዜ አገልግለናል፡፡ ከመዘምራንነት ውጪም በሀገረስብከት ደረጃ በተለያዩ የወጣት እንቅስቃሴዎች ተሳትፈናል፡፡ ዛሬ 2007 ዓ.ም. በተክሊል የመሠረትነው ቅዱስ ጋብቻ 14 ዓመታትን አስቆጥሯል ሁለት ወንዶች እና አንዲት ሴት ልጆችንም በማግኘት በጌታ በረከት ታድለናል፡፡

 

በዚህ ድረገጽ ካነበብነው እና ከሕይወት ልምዳችን ያገኘናቸውን በተለይ የትዳር ሕይወትን የተመለከቱ መጣጥፎችን እየተመካከርን እናቀርባለን፡፡  የትዳር ሕይወትን አስመልክቶ አስተማሪ የሚሆን ጽሁፍ ለማዘጋጀ የሚያስችል ትምህርት እና ሥልጠና የለንም ቢሆንም ግን በሕይወታችን ያጋጠሙንን ልምዶች ለሌሎች ብናካፍል ይጠቅማል ብለን ስለምናስብ ይህነንን ድረገጽ አዘጋጅተናል፡፡ በቀናነት የተፈጸመ ተግባር አድርጋችሁ ውሰዱልን፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ የሰፈሩ ቁም ነገሮች ጠቃሚ ሆነው ቢገኙ እና ለሌሎች ወዳጆቻችሁ በማናቸውም ዓይነት የማሰራጫ መንገዶች ለማጋራት ብትፈልጉ በነጻነት መጠቀም ትችላላችሁ፡፡  ግን ግን ሌሎች ይህንን ድረ ገጽ በመጎብኘት የበለጠ በረከት እንዲያገኙ እና ለእኛም መጸለይ እንዲችሉ መረጃዎቹን ከእኛ ድረ ገጽ ያገኛችኋቸው መሆኑን  በጨዋነት መጠቆምን አትዘንጉ፡፡የሁላችሁም ጸሎት አይለየን፡፡

 

ድረገጻችንን ስለምትጎበኙልን እና አስተያየቶቻችሁን ስለምታደርሱን እግዚአብሔር ይስጥልን፡፡

 

ሀብታሙ አብርደው

ወይንሸት ደምሴ

bottom of page