top of page


መሸፈኛ
ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 3 ብዙውን ጊዜ የሰው ልጅ ነገሮች ሁሉ የተበላሹበት ምዕራፍ ተደርጎ ይወሰዳል። ሆኖም ኝ በዚያ ውድቀትና ሀፍረት ውስጥ አስቀድሞ የተገለጠው የምስራች (የወንጌል) ብርሃን ምሥጢር ይገኛል። አዳምና ሔዋን ኃጢአት በሠሩ ጊዜ መጀመሪያ የተሰማቸው ስሜት ሀፍረት ነበር። ያደረጉትም ነገር የወደቀውን የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ምላሽ ነበር፤ ተሸሸጉ። የበለስ ቅጠሎችን ሰፉ። በራሳቸው ጥረት ሃፍረታቸውን ለመሸፈን ሞከሩ። ገና የእግዚአብሔርን ድምጽ እንኳን ከመስማታቸው በፊት፣ የሰው ልጅ ራሱን ከሃፍረቱ ለመሸፈን ጥረት መጀመሩን እንመለከታለን። ቀጥሎ የሆነው ነገር ግን እጅግ አስገራሚ ነው። እግዚአብሔር የእነርሱን የበለስ ቅጠል አልተቀበለም። መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር፦ “እግዚአብሔር አምላክ ለአዳምና ለሚስቱ የቁርበትን ልብስ አደረገላቸው፤ አለበሳቸውም”


"ከእሳቱ የተለየ ፍም አይሞቅም"
ሀብታሙ አብርደው በጡረ ከጥቂት ሳምንታት በፊት “ሰዎች ለምን ከቤተክርስቲያን ይርቃሉ?” የሚል ጥያቄ በገጼ ላይ አጋርቼ ነበር። ሰሞኑን አንድ ሰው ወደ እኔ ቀረብ ብሎ እንዲህ አለኝ፦ "ያጋራኸውን ጽሁፍ አይቼዋለሁ። እኔ እኮ አሁንም እግዚአብሔርን እወደዋለሁ፤ የራቅኩት ከቤተክርስቲያን እንጂ ከእግዚአብሔር አይደለም።" አለኝ። ምክንያት ያለውንም ይዘረዝርልኝ ጀመር። በቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ ሰዎች የሚያደርጉትን ነገር እርሱ ወደቢተክርስቲያን እንዳይመጣ እንዳደረገውም አስረዳኝ። እኔም ሌላ ጥያቄ አቀረብኩለት፦ "ለመሆኑ አንተ ፍጹም ነህን?" እርሱም "በየሰንበቱ እና በዓላቱ ወደ ቤተክርስቲያን ባልሄድም፣ ከሚያዘወትሩት ግን ሳልሻል አልቀርም" ሲል መለሰልኝ። ቤተክርስቲያን የተሰራችው ለፍጹማን አይደለም። ቢሆን ኖሮ ማንም የመግባት ብቃት ባልነበረው ነበር


“ኤል ሮኢ” የሚያየን አምላክ
ሀብታሙ አብርደው በጡረ ሰዎች በሚገፉባቸው እና ረዳት የለሽ የሆኑ በሚመስላቸው ሥፍራዎች ሁሉ የአጋር ታሪክ ይገለጣል። አጋር በአብርሃም ቤት ውስጥ የምትኖር ግብፃዊት አገልጋይ ነበረች፤ ከቤተዘመዶቿ እማ ከቀየዋ ርቃ፣ ተገልላና ምርጫ አጥታ የኖረች ናት። ምንም ነገር በእርሷ ፈቃድ አይደረግላትም አይደረግባትም። ውሳኔዎች ያለ እሷ ስምምነት ከበላዩዋና በዙሪያዋ በሚኖሩ ሰዎች ነበር የሚወሰኑት። ለራሷ ባልሆነ ዓላማ ጥቅም ላይ ውላ፣ በማትፈለግበት ጊዜ ደግሞ የተገፋች ነበረች፣ አጋር ብዙ የተገፉ ነፍሳት እንደሚያደርጉት ከሥቃይ፣ ከፍርሃትና መልስ ከሌላቸው ጥያቄዎች በቀር ምንም ሳትይዝ ራሷን በስደት ጎዳና ላይ አገኘችው። በስደት ወደ በረሃ ስትገባ የተሸከመችው ረሃብንና ድካምን ብቻ አልነበረም፤ መገፋትንና ያለመታየት ሕመምን ጭምር ነበር። ይሁን እንጂ፣ በዚያው
bottom of page