top of page
Website-Backgrounds-For-Desktop.jpg
ልባም_ሰው_logo-no bg.png

ሰው

ልባም

ልባም ሰው

ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በዓለት ላይ የሠራ ልባም ሰውን ይመስላል። 

ማቴ. 7፥24 

ቅድስት ቤተሰብ

  • Facebook

የዚህ ድረገጽ ባለቤቶች ሀብታሙ አብርደው እና ወይንሸት ደምሴ ነን፡፡ ሁለታችንም ከጠንካራ ካቶሊካውያን ቤተሰቦች ተወልደን በካቶሊካዊት ሥርዓት ተጠምቀን ቅዱሳት ቁርባንን፣ ሜሮንን እና የተክሊልን ምሥጢራት በአዲስ አበባ ልደታ ማርያም ቁምስና ካቴድራል ተቀብለናል፡፡ በቁምስናችን በመዘምራንነት ለረጅም ጊዜ አገልግለናል፡፡ ከመዘምራንነት ውጪም በሀገረስብከት ደረጃ በተለያዩ የወጣት እንቅስቃሴዎች ተሳትፈናል፡፡ ዛሬ 2007 ዓ.ም. በተክሊል የመሠረትነው ቅዱስ ጋብቻ 13 ዓመታትን አስቆጥሯል ሁለት ወንዶች እና አንዲት ሴት ልጆችንም በማግኘት በጌታ በረከት ታድለናል፡፡ በዚህ ድረገጽ ካነበብነው እና ከሕይወት ልምዳችን ያገኘናቸውን በተለይ የትዳር ሕይወትን የተመለከቱ መጣጥፎችን እየተመካከርን እናቀርባለን፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ የሰፈሩ ቁም ነገሮች ጠቃሚ ሆነው ቢገኙ እና ለሌሎች ወዳጆቻችሁ በማናቸውም ዓይነት የማሰራጫ መንገዶች ለማጋራት ብትፈልጉ በነጻነት መጠቀም ትችላላችሁ፡፡  ግን ግን ሌሎች ይህንን ድረ ገጽ በመጎብኘት የበለጠ በረከት እንዲያገኙ እና ለእኛም መጸለይ እንዲችሉ መረጃዎቹን ከእኛ ድረ ገጽ ያገኛችኋቸው መሆኑን  በጨዋነት መጠቆምን አትዘንጉ፡፡ የሁላችሁም ጸሎት አይለየን፡፡

 

ድረገጻችንን ስለምትጎበኙልን እና አስተያየቶቻችሁን ስለምታደርሱን እግዚአብሔር ይስጥልን፡፡

 

ሀብታሙ አብርደው

ወይንሸት ደምሴ

ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ቤተሰብን የሰው ልጅ ህብረተሰብ መሰረት አድርጋ ትቆጥረዋለች። በቤተሰብ ውስጥ የሚፈጠረው ፍቅር፣ አክብሮት እና እምነት ለግለሰብ እድገት እና ለማህበረሰብ ሰላም ትልቅ ሚና ይጫወታል ብላ ታምናለች።

ጋብቻ ቅዱስ ህብረት ነው

ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጋብቻን በአምላክ የተቋቋመ ሣልሣዊ ቅዱስ ህብረት አድርጋ ትቆጥረዋለች። ጋብቻ የወንድና የሴት ጥምረት ብቻ ሳይሆን ከክርስቶስ ጋር ያለንን አንድነት የሚያመለክት ነው

ቤተሰብ የሕይወት ምንጭ ነው

ቤተሰብ አዳዲስ ሕይወቶች የሚፈጠሩበትና የሚያድጉበት ቦታ ነው። በዚህም የሰው ልጅ ዘር ይቀጥላል

ቤተሰብ የእምነት ትምህርት ቤት ነው

ልጆች የመጀመሪያውን የእምነት ትምህርት የሚያገኙት በቤተሰብ ውስጥ ነው። በቤተሰብ ውስጥ ልጆች ስለ አምላክ ይማራሉ፣ ጸሎትን፣ ጾምን እና ልግስናን ይማራሉ። ለሌሎች ያላቸውን ፍቅር ያሳድጋሉ እና በጎ ሥራዎችን ይለማመዳሉ

አስተምህሮዎች

ጣዕመ ዝማሬዎች ​

bottom of page